የባለአክሲዮኞች 12ኛ አስቸኳይና 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ጥሪ

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 12ኛ አስቸኳይና 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ታህሣስ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ከጧቱ 4፡00 ጀምሮ ይደረጋል፡፡ ስለዚህ እርስዎም በዕለቱ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጥሪያችንን እያቀረብን የዕለቱን አጀንዳዎች ከዚህ በታች በዝርዝር እንገልፃለን፡፡

አጀንዳዎች፡-

የመደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

  • የ2022/2023 የሥራ አፈፃፀም የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥና ማጽደቅ
  • የ2022/2023 የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማድመጥና ማጽደቅ
  • የ2023/2024 የበጀት ዕቅድ ላይ መወያየትና ማጽደቅ
  • የተቋሙን 2023/2024 ሂሳብ ለመመርመር የውጭ ኦዲተሮች አበላቸውን ለመወሰን
  • ለቦርድ አባላት የድካም ዋጋ ክፍያን ስለመወሰን
  • የነባር ባለአክሲዮን ድርሻን በፍ/ቤት ውሳኔ መሠረት ለወራሾች መተላለፉን ማጽደቅ

አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ

  • 1. ከተጠራቀመ ትርፍ የተቋሙን ካፒታል ስለማሳደግ
  • 2. የተቋሙን መመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ስለማጽደቅ